Back to Top
30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ Screenshot 0
30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ Screenshot 1
30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ Screenshot 2
30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ Screenshot 3
Free website generator for mobile apps; privacy policy, app-ads.txt support and more... AppPage.net

About 30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ

በአላህ ስም በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው
የአላህ ሰላትና ሰላም ከፍጡራን ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነብያችን (ﷺ) ላይ ይውረድ።

ይህ አፕ ምርጥ የሆኑትን የነብያችን ﷺ ባልደረቦች ታሪክ በአጭሩ አካቶ ይዟል።
ሶሀቦች ቁርአንን የህይወታቸው ብርሀን አድርገው ይዘውታል። የኢስላምን መርሆችና አስተምህሮቶች ወደ ህይወት ለውጠዋል። በስነ ምግባር ምጥቀት ስፋትና በአላማ ፅናት እንዲሁም በመልካም ስብዕና ከፍተኛ ደረጃ ለመድረስ በቅተዋል ።
ነብዩም(ﷺ) እንዲህ ሲሉ አወድሰዋቸዋል
"ከሁሉም ምርጡ ትውልድ እኔ የምገኝበት ትውልድ ነው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው ፣ ከዚያም የሚቀጥለው …"
ታላቁ ሶሀባ ዐብደላህ ዒብነ መስዑድ የሶሀቦችን ገድል በዘከሩበት ንግግራቸው እንዲህ ይሉናል፦
"አረአያ ሊሆን የሚችል ስብዕና የሚሻ ካለ የመልዕክተኛው ባልደረቦች ብቻ ናቸው አርአያ ሊሆኑ የሚችሉት እናም የሶሀባ ትውልድ አባላት። ምክንያቲም እነሱ ከማንም በላቀ ሁኔታ የጠለቀ ዕውቀት ባለሀብቶች ነበሩና። ቀጥተኛውን ጎዳና መርተዋል። አላህ ለመልእክተኛው ባልደረባነት አጭቷቸዋል ። የዚህን ዲን ታላቅ አደራ ተሸክመዋል። ማንነታቸውን እወቁ ፣ፈለጋቸውንም ተከተሉ ፣ ቀጥተኛውን የህይወት መንገድ የተከተሉ ሰወች ነበሩና።
በየትኛውም ቦታና ጊዜ የምንገኝ ሙስሊሞች የዚያ ድንቅ ትውልድ ፤የዚያ ቁርአናዊ ማህበረሰብ አባላት አርአያነት እንደሚያስፈልገን ግልፅ ነው።ከሶሀባ ትውልድ ታሪክ በጣም ብዙ እንማራለን።ከምርጥ ስብእናቸው የጠራ ምንጭ እንጎነጫለን ። በህይወት ውስጥ ያደረጉት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ለህይወት ጉዟችን ብርሀን ነው ። የማንነታችን መለያ ነው…"።ከቀደምቶች ታሪክ እራሳችንን እንድናስተምር ይህ የሶሀበች ታሪክ የሚለው አፕ አስተማሪ ይሆናል ብለን እናስባለን።
በዚህ አፕ ታሪካቸው ያልተጠቀሱ ብዙ ሶሀቦች አሉ፤ በአላህ ፍቃድ በየግዜው የሌሎችም ሶሀቦች ታሪኮችን አካተን አፑን በየግዜው እናድሰዋለን፣ ከእርሶ የሚጠበቀው ይህን አፕ በየግዜው ማዘመን/Update ማድረግ ነው።

ከአጅሩ ተቋዳሽ ይሆኑ ዘንድ አንብበው ለሌሎችም ያጋሩ።

ይህ ስራችን የተከበረው የአላህን ፊት ተፈልጎበት የተሰራ እንዲሆን እንዲሁም ታሪኩን ከተለያዩ ምንጮች ላሰባሰቡ ፀሐፊዋች ለኛም በዚህ ስራ ለተባበሩንም በሞት ለተለዩንም ይህንን ስራ ለሚያሰራጩትም ከሁላችንም  ይቀበለን ዘንድ አላህን እማፀነዋለሁ።

በአላህ ፍቃድ ሌሎች ጠቃሚ አፖችን አዘጋጅተን በቀጣይ እናደርሳችኃለን።
________________
የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል - ከናንተ ውስጥ መጥፎን ነገር ያየ በእጁ ይቀይር ካልቻለ በምላሱ ካልቻለ ደግሞ በልቡ ይጥላ ይህ ግን (በልብ ብቻ መጥላት) ደካማ ኢማን ነው" (ሙስሊም ዘግበውታል)
ወንድም እህቶቼ ታሪኩን በምታነቡበት ግዜ ከቁርአን ከሀዲስ የተጨመረ ወይም የተቀነሰ ነገር ካገኛችሁ በአድራሻዬ አድርሱኝ።
ስህተቴን ላረመኝ ሰው አላህ ይዘንለት።

አላህ ሆይ!ጠቃሚ እውቀትን ከተግባር ጋር ወፍቀን መጨረሻችንንም አሳምርልን አሚን! ከተሳሰትኩ ከነፍስያዬና ከሸይጧን ሲሆን ሐቅን ከገጠምኩኝ ከአላህﷻ ነው።

የአፑ አዘጋጅ አብዱራሂም ማህሙድ

※ከዚህ በፊት ያዘጋጀነውን የነብያት ታሪክ አፕ በሚከተለው ሊንክ መጫን ይችላሉ፦
https://play.google.com/store/apps/details?id=qissa.anbia.hudasoft

Similar Apps

30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ

30+ የሶሀቦች ታሪክ | ሐያቱ ሶሀባ

0.0

በአላህ ስም በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው የአላህ ሰላትና ሰላም ከፍጡራን ሁሉ ምርጥ...

የነብያት ታሪክ story of prophets

የነብያት ታሪክ story of prophets

0.0

በአላህ ስም በጣም አዛኝና ሩህሩህ በሆነው የአላህ ሰላትና ሰላም ከፍጡራን ሁሉ ምርጥ...

ተፍሲር ጁዝእ ዐመ በድምፅ

ተፍሲር ጁዝእ ዐመ በድምፅ

0.0

የዐመ ጁዝ ተፍሲር በሸይኽ አወል ቢን አህመድ አቡ አማር አል ከሚሴ+በቂ ማብራሪያ...

አል-ኡሱሉ ሰላሳ ደርስ ቁጥር (01)

አል-ኡሱሉ ሰላሳ ደርስ ቁጥር (01)

0.0

ይህ የሞባይል መተግበሪያ የአል ኡሱሉ ሰላሳ ደርስ በኡስታዝ ሙሀመድ ቢን አብዱል ጀባር...

መትን አርበዒነ አን-ነወዊ ቁጥር አንድ

መትን አርበዒነ አን-ነወዊ ቁጥር አንድ

0.0

ይህ የሞባይል መተግበሪያ የአርበዒነ ነወዊ ደርስ ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ መልኩ ከክፍል 1–59...

ሹሩጡ ሰላት ደርስ

ሹሩጡ ሰላት ደርስ

0.0

ይህ የሞባይል መተግበሪያ በኡስታዝ ሙሀመድ ቢን አብዱል ጀባር (خليك)ሀፊዘሁሏህ የተሰጠውን የመትን ሹሩጡ...

author
ما شاء الله
Bderia Awol
author
አላህ ጀነትን ያስገባችሁ አቦ
Hussen Derese
author
Mashallah jezakumulahu keyr
Merem Ebrahim
author
ወላሂ እስካሁን ስፈልገው ነበርኩ አልሐምዱሊላህ በናንተ ሰበብ አገኘሁት አልሐምዱሊላህ!!!!! ኸይር ጀዛችሁን አረሕማን ይክፈላችሁ
Redi Seman
author
Amazing app
Hayat Nuredin
author
በጣም ጥሩ ነው ማሻ አላህ በርቱ
Maqi Meqiya