AppPage.net

Screenshots

  • የእንስሳት ህይወት - Animals Life screenshot 1
  • የእንስሳት ህይወት - Animals Life screenshot 2
  • የእንስሳት ህይወት - Animals Life screenshot 3
  • የእንስሳት ህይወት - Animals Life screenshot 4
  • የእንስሳት ህይወት - Animals Life screenshot 5
  • የእንስሳት ህይወት - Animals Life screenshot 6
  • የእንስሳት ህይወት - Animals Life screenshot 7
  • የእንስሳት ህይወት - Animals Life screenshot 8

About የእንስሳት ህይወት - Animals Life

ይህ የእንስሳት ህይወት - Animals Life የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ በልዩ የመረጃ ማዕከል - Liyu Multimedia የተሰራ ሲሆን አዋቂዎችና በተለይም ልጆች ጠቅላላ ዕውቀት እንዲያገኙ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ የመማሪያ አፕልኬሽን ነው፡፡ ዜጎች በቀላል የአማርኛ ቋንቋ ስለእንስሳት መረጃ አግኝተው ዕውቀታቸውን እንዲያሰፉ የሚያግዝ መተግበሪያ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ለእንስሳት ተገቢ የሆነ እንክብካቤ እንድናደርግ የእንስሳት ተፈጥሮና ባህሪ ምን እንደሚመስል የሚያስቃኝ የዲጅታል መሳሪያ ነው፡፡

በዚህ አፕልኬሽ ውስጥ ሰባት አይነት መደብ በመፍጠር - የዕርባታ እንስሳት፣ ለማዳ እንስሳት፣ የዱር እንስሳት፣ ተሳቢ እንስሳት፣ የአዕዋፋት ዝርያ፣ የባህር እንስሳትና አነስተኛ ነፍሳት በማለት ከ100 በላይ እንስሳት መረጃቸው ተቀምጧል፡፡ በስም ብቻ የምናውቃቸው እንስሳት ኖረው መልካቸው ምን እንደሚመስል የማናውቃቸው፣ በመልክ አውቀናቸው ነገር ግን ስማቸውን የማናውቃቸው፣ በአማርኛ አውቀናቸው በእንግሊዘኛ ቋንቋ የማናውቃቸውንም በቀላል ሁኔታ እንድናውቃቸው ተደርጎ የተሰራ አፕልኬሽን ነው፡፡

በአለማችን ላይ በርካታ እንስሳት አሉ፡፡ የሰው ልጅ ራሱ እስካሁን ድረስ ገና አውቆ ያልጨረሳቸው እንስሳት በተለይም የአዕዋፋት ዝርያና የባህር እንስሳት በርካታ ናቸው፡፡ እናም በዚህ መተግበሪያ ላይ እኛም እንዲሁ መጠነኛ ዕውቀት ለማስጨበጥ ያህል ብቻ የተወሰኑትን የምናውቃቸውን በተቻለ መጠን አቅርበናል፡፡ በእንስሳት ጥናት ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተጨማሪ መረጃ ቢኖራቸውም እኛ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለግንዛቤ ያህል ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ወደ አማርኛ በመተርጎም ለህብረተሰባችን አቅርበናል፡፡

ይህንን የሞባይል መተግበሪያ ማንኛውም የአንድሮይድ ስልክ ተጠቃሚ በቀላሉ ሊጠቀምበት የሚችል ሲሆን የእንስሳት አርብቶ አደሮች፣ በዱር እንስሳት ጥበቃ ላይ የተሰማሩ አካላት፣ በእንስሳት ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች፣ የእንስሳት ጎብኝዎች ማለትም ቱሪስቶች፣ በተለያየ የትምህርት ደረጃ ላይ የሚማሩ ተማሪዎች፣ ለእንስሳት ፍቅር ያላቸው ሰዎች፣ ለእንስሳት ምንጊዜም ልዩ ቅርበትና አመለካከት ያላቸው ህፃናት፣ እንዲሁም ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎች በቀላሉ አፕልኬሽኑን ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

ታዲያ ግን ይህንን መረጃ በመጠቀም ለእንስሳት የምናደርገውን እንክብካቤ በማሳደግ የተሻለ ህይወት እንዲኖራቸው ማስቻል የሁላችን ድርሻ ነው፡፡ በዕውቀት ማነስ የተነሳ እንደ ቀላል የምናያቸውን እንስሳት ጎድተናቸው ሊሆን ይችላል፣ ዛሬም ቢሆን ልንጎዳቸው እንችላለን ነገር ግን አስተሳሰባችንን በማስፋት የተሻለ ስራ ልንሰራ ይገባል፡፡ ይህንን የአመለካከት ችግር በጋራ ልንቀርፈው እንችላለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለዕርባታም ሆነ ለምርምር የምንጠቀማቸውን እንስሳት ይበልጥ በተሻለ በመያዝና በመከታተል ትርፋማ መሆን የምንችልበትን መንገድ መፍጠር ይኖርብናል፡፡

User reviews

Samson Biyadglgne
Samson Biyadglgne
It show life is given for all
Jimmy brhanu “jari” brhanu
Jimmy brhanu “jari” brhanu
አንበሳ ነህ ወንድሜ በርታ. ቆቅ ነህ. ለወደፊት ለልጆች ለታዳጊ ዎች የሚሆን ነው

Alternatives to የእንስሳት ህይወት - Animals Life

Looking for apps like የእንስሳት ህይወት - Animals Life? Here is 1 similar Android app on Google Play.

የእንስሳት ህይወት - Animals Life vs. alternatives
App Rating Price Installs Last updated Compare
የእንስሳት ህይወት - Animals Life – Free 10+ Aug 8, 2023
Liyu Muya: Directory & Profile 4.3 / 5 Free 1,000+ Jul 13, 2024 Compare

Compare የእንስሳት ህይወት - Animals Life with the top alternatives: ratings, updates, ASO score and keyword gaps →

Similar apps on Google Play