Metsihafe Sinksar መጽሐፈ ስንክሳር
የቅዱሳንን ተጋድሎ፣ ክርስቲያናዊ ፅናትና ግብር በአጠቃላይ ገቢረ ገድላቸወንና ትሩፋታቸውን የሚዘክር መጽሐፍ ነው፡፡
About Metsihafe Sinksar መጽሐፈ ስንክሳር
መጽሐፈ ስንክሳር አስተጋብአ (ሰበሰበ) ከለው የግእዝ ቃል የወጣ ሲሆን አስተጉቡእ (ስብስብ) ማለት ነው ፡፡ ጥርቅምቅም ውጥንቅጥ የተቀያየጠ መድበል የተደባበለ ነገር ማለት ነው ።
የሥላሴን አንድነትና ሦሥትነት÷ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቅድመ ዓለም ያለእናት ከበሕርይ አባቱ ከአብ÷ ድኅረ ዓለም ያለአባት ከእመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ መወሐዱን÷ የመላእክትን ማዕርግና ሹመት የሚያስረዳ የነቢያትንና የሐዋሪያትን የጻድቃንንና የሰማዕታትን የደናግልንና የመነኮሳትን ምግባር መከራና እረፍት ከዕለት እስከ ዓመት የሚነገር መጽሐፍ ነው፡፡ የቤተ ክሲያንን ታሪክ÷ የመቤታችንን ዜና የልጇንም በጎ ሥራ ኹሉ በሰፊው ይናገራል። ትርጓሜውም በጽርእ የተሰብሰበ ስብስብ ማለት ነው። የቅዱሳን ነቢያትንና ሐዋርያትን÷ የቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታትን÷ ሀይማኖታዊ ተጋድሎ÷ ክርስቲያናዊ ፅናትና ግብር በአጠቃላይ ገቢረ ተአምራታቸውን÷ ገድላቸወንና ትሩፋታቸውን የሚዘክር ዕለተ መታሰቢየቸውንም የሚጽሐፍ መጽሐፍ ነው፡፡ ጠቅለል ባለ ቋንቋ መጽሐፈ ስንክሳር ዝክረ ቅዱሳን መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ከመጻሕፍተ ብሉያትና ሐዲሳት÷ ከገድላትና ድርሳናት የተቀዳ በቤተ ክርስቲያን በየቀኑ የሚነበብ ዜና ቅዱሳን ነዉ፡፡
የመጽሐፉ ስም ከዓመት እስከ ዓመት የሚነበብ የቅዱሳን ዜና ከየገድላቸው ባጭር ባጭር ቃል የተሰበሰበ እሉድ ምእላድ እስትጉቡእ ማለት ነው፡፡
እስከ ዓመት በአሉት ዕለታት የሞቱ የነቢያትን የሐዋርያትን የሰማዕታትን የጻድቃንን የመነኮሳት የደናግል በእግዚአብሔር ስም ለዐረፉ ታሪካቸውና ገድላቸው የተጻፈበት ወይም የሞቱበትንም ቀን የሚዐሳስብቀ መጽሐፈ ስንክሳር መድበል።
Metsihafe Sinksar መጽሐፈ ስንክሳር details
Metsihafe Sinksar መጽሐፈ ስንክሳር is a free Books & Reference app for Android with 5,000+ installs on Google Play and a 3.9/5 average rating from 19 ratings. It was released on July 31, 2019 and last updated on July 31, 2019. It requires Android 4.0 or later.
- Category
- Books & Reference
- Rating
- 3.9 / 5 (19 ratings)
- Installs
- 5,000+
- Price
- Free
- In-app purchases
- No
- Ads
- No ads
- Current version
- 1.0
- Size
- 7.8M
- Requires Android
- 4.0 and up
- Content rating
- Everyone
- Released
- July 31, 2019
- Last updated
- July 31, 2019
Similar Apps
Mezgebe Haymanot መዝገበ ሃይማኖት
Mezgebe Haymanot is a mobile application with huge Ethiopian Orthodox Tewahedo Church...
Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ ፹፩
በይዘቱ ተሟልቶ በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የተዘጋጀ የመጀመሪያው ምሉዕ መጽሐፍ ቅዱስ...
Mezgebe Tselot መዝገበ ጸሎት
Mezgebe Tselot is the great Ethiopian Orthodox Tewahedo Church collection of prayer...
Mezgebe Tselot መዝገበ ጸሎት
Theme • Material Design color schemes. • Setting for Night mode and...
Melka Kidusan መልክዐ ቅዱሳን
መልክአ ቅዱሳን (የቅዱሳን ውዳሴ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘወትር ወይም...
Mezgebe Tselot መዝገበ ጸሎት
መዝገበ ጸሎት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘወትር የሚጠቀሙባቸውን የጸሎት የተለያዩ ዓይነት...