ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖትና በቅብዐት እምነት መካከል ያለውን ልዩነት የሚያስረዳ መጽሐፍ ነው ።
About ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk
«ፍኖተ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ» በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት፣ ቀኖና እና ትውፊት መሠረት ዶግማ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ከ፲፪ መጻሕፍት በላይ ተካተውበት የቀረበ የመጻሕፍት መድብል ነው።
ይህ የመጻሕፍት መድብል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትርጓሜ ሊቃውንት የተራቀቁባቸውን እና የተጠበቡባቸውን ሲወርዱ ሲወራረዱ ለእኛ የደረሱ የትርጓሜ መጻሕፍት የተካተቱበት ነው። በሦስት ዐበይት ክፍሎች የተመደቡ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ያካተተው ይህ መድብል ምክርና ተግሳጽንም የያዘ ስለሆነ ብዙዎች እንደሚወዱት ተስፋ እናደርጋለን። በአዘጋጁ ታትመው የቀረቡና እና ለኅትመት ዝግጁ የሆኑ መጻሕፍትም የተካተቱበት ስለሆነ ልዩ ያደርገዋል። በአዘጋጁ ከቀረቡ መጻሕፍት መካከል በቅብዐት ምንፍቅና አማኞች ለተጻፉ መጻሕፍት ተገቢ ምላሽ የተሰጠባቸውን «ደብረ አሚን - የሃይማኖት ተራራ» እና «ፍኖተ ጽድቅ - የእውነት ጎዳና» አካተናል። ከዚህ በተጨማሪም አዘጋጁ የጻፋቸው የተለያዩ ወጎች፣ ትምህርቶችና ግጥሞችም ምክርና ተግሳጽን በስፋት አካተው ቀርበውበታል። ከእግዚአብሔር ለምን እንርቃለን? እግዚአብሔርስ ከእኛ ለምን ይርቃል? የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ የሚመልስ እና ወደ ንስሐ የሚመራ «ለምን ርቀህ ቆምህ?» የተሰኘው የአዘጋጁ መጽሐፍም በዚሁ መድብል ውስጥ የተካተተ ነው። እነዚህ የአዘጋጁ መጻሕፍት ገበያ ላይ የማይገኙ መሆናቸው ይህን መተግበሪያ ልዩ ያደርገዋል።
ይህ መተግበሪያ በተጨማሪነት ቤተ ክርስቲያናችን ከዓመት እስከ ዓመት የምትገለገልባቸውን ድንቅ መጻሕፍት ሃይማኖተ አበውንና መጽሐፈ ስንክሳርን ያካተተ ነው።
ይህ መተግበሪያ የያዛቸው መጻሕፍት ዝርዝር
፩. የአንድምታ ትርጓሜ ክፍል
- የጸሎተ ሃይማኖት አንድምታ ትርጓሜ።
-የውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።
- የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።
- የአራቱ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ።
፪. የአዘጋጁ መጻሕፍት ክፍል
- ደብረ አሚን
- ፍኖተ ጽድቅ
- ለምን ርቀህ ቆምህ?
- አማኞችን ማጽናትና ማበርታት
- ወጎች
- ትምህርቶች
- ግጥሞች
፫. ሌሎች መጻሕፍት ክፍል።
- ሃይማኖተ አበው
- መጽሐፈ ስንክሳር
- ፍኖተ እግዚአብሔር
ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk details
ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk is a free Books & Reference app for Android with 5,000+ installs on Google Play and a 4.6/5 average rating from 27 ratings. It was released on February 2, 2019 and last updated on October 22, 2019. It requires Android 4.0 or later.
- Category
- Books & Reference
- Rating
- 4.6 / 5 (27 ratings)
- Installs
- 5,000+
- Price
- Free
- In-app purchases
- No
- Ads
- No ads
- Current version
- 2.0
- Size
- 8.6M
- Requires Android
- 4.0 and up
- Content rating
- Everyone
- Released
- February 2, 2019
- Last updated
- October 22, 2019
What’s new in ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk
በዚህ ዕትም የሚከተሉት መጻሕፍት ተካተዋል። ፩. ጸሎተ ሃይማኖት አንድምታ ትርጓሜ ፪. ውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ ፫. ፬ቱ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ ፬. ሃይማኖተ አበው ፭. መጽሐፈ ስንክሳር ፮. ደብረ አሚን ፯. ወጎች ፰. ትምህርቶች ፱. ግጥሞች ፲. ፍኖተ እግዚአብሔር ፲፩. ሊሎችም የዲያቆን መልካሙ በየነ ሥራዎች ተካተዋል።
Version 2.0 · Updated October 22, 2019
Similar Apps
Mezgebe Haymanot መዝገበ ሃይማኖት
Mezgebe Haymanot is a mobile application with huge Ethiopian Orthodox Tewahedo Church...
Mezgebe Tselot መዝገበ ጸሎት
Mezgebe Tselot is the great Ethiopian Orthodox Tewahedo Church collection of prayer...
Melka Kidusan መልክዐ ቅዱሳን
መልክአ ቅዱሳን (የቅዱሳን ውዳሴ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘወትር ወይም...
Geez Amharic Dictionary የግእዝ መ
The offline Geez and Amharic dictionary application explains the meaning of Geez...
Amharic Dictionary
ማሳሰቢያ: ይህ አፕሊኬሽን ከጫኑት በኋላ ሃምሳ ብር ያስከፍላል።The offline Amharic - Amharic...
Geez Amharic Bible መጽሐፍ ቅዱስ በግ
በይዘቱ ተሟልቶ በሦስት ቋንቋዎች (በግእዝ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ) የተዘጋጀ የመጀመሪያው ምሉዕ መጽሐፍ ቅዱስ...