It is a spiritual app for deacons as well as voice lessons that are used in some way for priests
ቃለ ስብሐት የአብነት ትምህርት መማር ለሚፈልገ ሁሉ ትልቅ እገዛ የሚያደርግ መተግበሪያ ሲሆን ለተማሩት የረሱትን ለማስታወስ በተለያየ ምክንያት ወደ አብነት መምህራን ሄደው መማር ላልቻሉ ተማሪዎቸ ደግሞ (ይሄ ሲባል ግን ጊዜ እያላቸው እና በአቅራቢያቸው መምህራን እያሉ ሄደው የማይማሩትን አይመለከተም) የበኩሉን አስተዋጽዎ ያደርጋል ፤ እንዲሁም ተማሪዎች በሚማሩበት ወቅት ሪከርዱን እያዳመጡ ከመምህሩ ቢማሩ የመምህሩን ድካም እና የተማሪውን ጊዜ መቆጠብ ይቻላል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የዚሁ መተግበሪያ አንድ አካል የሆነ በከፍተኛ ሁኔታ በአብነት ተማሪዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈ “ቃለ ቅዳሴ” ተብሎ የተሰየመ የስርዓተ ቅዳሴ መጽሐፍ ይዘትም ከስርዓተ ቅዳሴ በተጨማሪ ፡- ተፈሥሒ ማርያም ፣ መልክዓ ስዕል ፣ እሴብሕ ጸጋኪ እንዲሁም የዜማ ምልክቶችን ሙሉ ቃላቸውን ከነ መገኛቸው እንዲሁም ሌሎችንም አስፈላጊ ነገሮች በአንድ ጥራዝ አሰባስቦ የያዘ መጽፍ ነው፡፡ነገር ግን መተግበሪያውም ሆነ መጽሐፉ የተዘጋጁት የተማሪዎችን ድካምና ጊዜ ለመቆጠብ ታስቦ እንጂ ያለ መምህራን በዚህ መተግበሪያ ብቻ መማር በቂ ነው ማለት እንዳልሆነ እንዲገነዘቡልን እንፈልጋለን፡፡
ወስብሃት ለእግዚአብሔር
እግዚአብሔር ያከበራችሁ መላእክትም ጻድቃንም ምስጋናዋን መፈጸም የማይቻላቸው እመቤታችንን ተአመር ለመስማት አይነ ልቡናችሁን...
መጻሕፍትን ለጸሎት ለትምህርት ለልዩ ልዩ አገልግሎት ማዋል በማህበራዊ ኑሮ ተፈላጊነቱ ከፍተኛ ነው...
Praise be to Mary the most Beloved and High, this is one...
አርጋኖን የተሰኘው መጽሐፍ ሊቁ እመቤታችንን በቅኔ ያመሰገነበት መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ እንደ...
Frequently Asked Questions(FAQ)
Created with AppPage.net
Similar Apps - visible in preview.