መሐረነ አብ ጸሎት በግእዝና አማርኛ ከነ ዜማው -ምእመናን በቀላሉ እንዲያነቡት እንዲረዱት እንዲሁም ዜማውን ለመለማመድ ያስችላል
የመሐረነ አብ ጸሎትን ያዘጋጀው ከ40 መጻሕፍት በላይን የደረሰውና ካልዓይ ቅዱስ ያሬድ ፥ ካልዓይ ቄርሎስ የተባለው ቅዱሱ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ ነው፡፡ ሲያዘጋጀውም ከተለያዩ ቅዱሳት መጻሕፍትና እንደ ቅዱስ ያሬድ ካሉ ሊቃውንት ድርሰቶች ኀይለ ቃላት ያላቸውንና ለጸሎት ተስማሚ የሆኑ ቃላትን እንደ ንብ ቀስሞ ነው ያዘጋጀው፡፡
፠ ቅዱሱ ያዘጋጀውም በመጽሐፈ ሰዐታት ድርሰቱ ላይ በስተመጨረሻ ከኪዳን በፊት እንዲደረስ አድርጎ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከዓመት እስከ ዓመት በየዕለቱ ኪዳን በሚደርስባቸው ማንኛውም የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክንና ገዳማት ‹‹የመሐረነ አብ ጸሎት››ም ከኪዳን በፊት ይደርሳል፡፡
፠ የመሐረነ አብ ጸሎት ከኪዳን በፊት ብቻ ሳይሆን፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት በዋይዜማው የሚደርስ፣ ለግል ጸሎት፣ ረሃብ ጦርነት፥ አባር ቸነፈር፥ ተስሕቦና ወረረሽኝ በሽታ እና የተለያዩ ችግሮች በመጡ ወቅት የሚደረስ ሲሆን ከእግዚኦታ ጋር አብሮ ስለሚባልም ‹‹የምሕላ ጸሎት›› በመባልም ይጠራል፡፡
፠ የጸሎቱ አደራረስም በመሪና በተመሪ (በቀኝና በግራ) በተራ ስለሆነ በጋራ የሚጸለይና ዜማው የሚመስጥ፤ የቃሉ አሰዳደርም የሚያስደንቅ፤ የያዘው ኀይለ ቃል እንባን የሚያስነባ ነው፡፡ በተለይም በገዳም ያሉ አባቶች በጋራ(በማኅበር)ና በግል ጸሎት ዕለት ዕለት ያደርሱታል፡፡
ይህን የጸሎት የምህላ ጸሎት ለምእመናን በቀላሉ እንዲያነቡት ፡ እንዲረዱት እንዲሁም ዜማውን እንዲለማመዱበት ታስቦ የተሰራ መተግበሪያ ነው።
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Application that have thousands of mezmurs/songs, teachings, arts...
An application designed to help users engage with the Ethiopian Orthodox liturgy...
መጽሐፈ ሰዓታት መተግበሪያ እጅግ ቀላል በሆነ መልኩ ሁሉንም ክፍሎች ያከተተ ሲሆን በውስጡ...
ይህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የተወሰዱ እና የሚወክሉ በሺዎች የሚቆጠሩ HD...
በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረኪዳን ግርማ የተሰጡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርቶች እና...
ይህ የግእዝ መማሪያ አፕሊኬሽን በውስጡ የተለያዩ ትምህርቶችን፡ የመድብለ ግስ ዝርዝር ከነ አርእስታቸው...
Created with AppPage.net
Similar Apps - visible in preview.