Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት

Contains ads
4.5
554 reviews
50K+
Downloads
Content rating
Everyone
Screenshot image
Screenshot image
Screenshot image
Screenshot image
Screenshot image
Screenshot image
Screenshot image

About this app

This APP contains more than 400 different Holy Pictures of Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Holy Saints, Holy Angels, Holy Fathers, Holy Mothers, and Holy Pictures of God with a List of Yearly, Monthly Holy Days which are celebrated in Orthodox Tewahedo Church and finally the app contains a list of biblical name and their meninges.

Please give attention that the Holy pictures which are found in this app are not the only one there are a lot of Saints which are not included in this APP.

በዚህ መተግበሪያ ውስጥ ከ400 በላይ የቅዱሳን ስዕላትን በማንኛውም ጊዜ ማግኘት እንዲችሉ ካለ ኢንተርኔት እንዲሰራ በመተግበሪያው ውስጥ ስእላቱ እንዲካተቱ ተደርጎዋል፡፡
ከቅዱሳኑ በረከት ረድኤት ይደርብን
አሜን!!!

ከዚህ በታች ያለው አቡነ ገብርኤል በ1990 ካሳተሙት “ክብረ ቅዱሳን» ከሚለው መጻሕፍ የተወሰደ ነው

የጥንቱና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚከተል ክርስቲያን ሁሉ ከቅዱሳት ሥዕሎች ሁለት ዐበይት ጥቅሞችን ያገኛል ይኽውም ትምህርትና ረድኤት ናቸው። ይልቁንም ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረው ቃለ እግዚአብሔር (አካላዊ ቃል) በኋለኛው ዘመን ሰውን ለማዳን ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተፀንሶ ከሥጋዋ ሥጋን ፣ ከነፍስዋ ነፍስን ነስቶ ከኃጢአት ብቻ በቀር ፍጹም ሰው ሆኖ በድንግልና የተወለደውና ተሰቅሎ በሞቱ ዓለሙን ማዳኑን በሥዕል ገልጾ ማቅረብ መስበክ፤ ማስተማር ነው። በዚህም መሠረት የጌታችንን የልደቱን ታሪክ፣ የጥምቀቱን ታሪክ፣ የስቅለቱን ታሪክ፣ የትንሣኤውንና የዕርገቱን ታሪክ በሥዕል ነድፎ ለምእመናን ማቅረብ ማለት የጌታችንን ወንጌለ መንግሥት መስበክና ማስተማር ማለት ነው ምክንያቱም ሥዕል ራሱበጉልህ የተጻፈ ጽሑፍ ማለት ነውና። ጌታችን ተወለደ፣ ተጠመቀ፣ ተሰቀለ ፣ ሞተ፣ ከሙታን ተለይቶተነሣ… የሚለው የወንጌሉ ታሪክ በሥዕል ማቅረብ ማለት ታሪኩን በጉልህ ጽፎ ማቅረብ ማለት ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች ተግሳጽ ሲጽፍ «የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፤ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር» ያለው ኢየሱስና ታሪኩን በሚገባ አውቀውትና ከልብም ተረድተውት እንደ ነበር ለመግለጽ ነው (ገላ.3፤ 1-2)

ስለዚህ ከላይ እንደተገለጸው ቅዱሳት ሥዕሎች በመመልከትና ልብ ብሎ በማንበብ (በማስተዋል) ታሪኩን በሚገባ ማወቅና መረዳት ስለሚቻል ፤ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ሥዕሎች የክርስትና ሃይማኖት አስተማሪዎችና አስረጂዎች መሆናቸውን መገንዘብ ተገቢ ነው።

ሁለተኛው ጥቅም ከቅዱሳት ሥዕሎች የሚገኘው ሌላው ዐቢይ ጥቅም ደግሞ ረድኤት (ርዳታ) ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በነበረበት በጣም ቅርብ የነበሩት የጥንት ክርስቲያኖች በጌታችን ሥዕል፣ በቅድስት ድንግል ሥዕልና በቅዱሳን ሥዕሎች ይማፀኑ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል ። በዘመናችን ተቆፍረው የተገኙ የጥንት አብያተ ክርስቲያናት ፍርስራሶችም በሥዕላተ ቅዱሳን መማፀን ጥንታዊ ትውፊት (ሥርዓት) እንደሆነ ያመለክታሉ ታሪክን መካድ ደግሞ አያትና ቅድመ አያትን መካድ ማለት ነው። ስለ ሥዕል ክብር የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ታሪክ ምስክር ነው። የታወቀው ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ አውሳብዮስ ኤጲስ ቆጶስዘቂሳርያ ስለ ጌታ ሥዕል አጀማመርና አመጣጥ ጽፎ ያቀረበውን ብፁእ አባ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ ዘሸዋበመጽሐፋቸው ጠቅሰውታል። አኛም የጥቅሱን ፍሬ ነገር ቀጥለን ጠቅሰነዋል።

«ንጉሥ ዐብጋር በዑር (ኤዴሣ ከተማ የአገሩ ንጉሥ በመሆን ጌታችን በነበረበት ዘመን ይኖር ነበረ፤ ስሙም (ልዑካን) ይባል ነበር። ዐብጋር ማለት በከለዳውያን ቋንቋ ቄሣር ማለት ነው። ዐብጋር በዚያ ዘመን በጠና ታሞ ነበር፤ የጌታችንን ተአምራት በዝና ሰምቶ ይፈውሰው ዘንድ ደብዳቤ ጽፎ ለጌታችን ላከለት፤ ጌታችንም ደብዳቤውን ከመልእክተኛው እጅ ተቀብሎ ካነበበው በኋላ «ሳያየኝ ያመነኝ ዐብጋር ብፁዕ ነው» ብሎ ዐብጋርን በማመስገን በሱ ስም እንዲፈውሰው ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዱን እንደሚልከለት በመግለጽ መልስ ላከለት። ነገር ግን ከጌታ ጋር ተገናኝቶ የተመለሰው የዐብጋር (ዩካማ) መልእክተኛ ሠዓሊ ስለነበር ከጌታችን ጋር ሲነጋገር ፊቱን በሥዕል ነድፎ (ሥሎ) ከደብዳቤው ጋር ይዞ ተመለሰ። ከዚያም አንደ ደረሰ ከጌታ የተላከውን ደብዳቤ ለታመመው ንጉሥ አነበበለት፤ ሥዕሉንም አሳየው። በዚያን ጊዜ በሽተኛው ንጉሥ የጌታችንን ቃል ከደብዳቤው ሰምቶና ሥዕሉንም በዓይኑ ተመልክቶ ወዲያው ከሕመሙ እንደ ተፈወሰ ታሪኩ ያስረዳል (አባ ጎርጎርዮስ፤ የኢ ኦ ተ ቤተ ክርስቲያንታሪክ 1974 ገጽ 119 120)።

ይኽው አውሳብዮስ ስለ ጌታችን ሥዕል የሰጠው ምስክርነት እንዲህ የሚል ነው «ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ደሙን እያንጠፈጠፈ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ጎልጎታ በሚጓዝበት ወቅት እያለቀሱ ከሚከተሉት ደጋግ ሴቶች መካከል ቬሮኒካ የተባለች ደግ ሴት የራስዋን መሸፈኛ አውልቃፊቱን አንዲያድፍበት (እንዲጠርግበት ስጌታ ወረወረችለት፤ ጌታችንም በደምና በላብ የተጠመቀውን ፊቱን ጠርጎ ሲመልስላት ሥዕለ ገጹ ማለት የፊቱ መልክ በሻሽዋ ላይ ታትሞ ቀረ» በማለት ከላይ የጠቀስነው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ይመሰክራል።

ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ደግሞ ወላዲተ አምላክ በነበረችበት ክፍለ ዘመን የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ የጌታን ታሪክ (ወንጌል) ሲጽፍ ስለ ወላዲተ አምላክም ብዙ ጽፎአል። በዚህ የያዕቆብ ወንጌል (ያዕቆብ ታሪክ) በተባለው የትውፊት መጽሐፍ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለመጀመሪያ ጊዜ የማርያምን ሥዕል መሃሉ ተጽፎአል።

አውሳብዮስ ኤጲስ ቆጶስ ዘቂሳርያና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች እንደ መሰከሩት የጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፣ ለወላዲተ አምላክ፣ ለቅዱሳን መላእክት፣ ለጻድቃንና ለሰማዕታት ሥዕሎች ከፍ ያለ ክብር እንዲደረግላቸውና የጸጋና የአክብሮት ስግደት እንዲቀርብላቸው ስታስተምር ኖራለች። ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት በሚጸልዩበት ቤተ ክርስቲያንና በቤታቸው በሚገኘው በግል ጸሎት ቤታችው የጌታችንን፣ የቅድስት ድንግል ማርያምና የቅዱሳንን ሥዕሎች በግድግዳው በመስቀልና የክብር ስግደት በማቅረብሲማፀኑባቸው ኖረዋል።

በዚሁ ሁኔታ የሥዕል ክብር በጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን እንደ ተጠበቀ አስከ ስምንተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ከቆየ በኋላ ሳይታሰብ በድንገት ከክርስቲያኖቹ መካከል ጥቂቶች ሰዎች የሥዕልን ክብር በመቃወም ተነሡ። በዚሁ ምክንያት በሮምና በቢዛንታይን ግዛቶች ከባድ ክርክርና ሁከት ተቀሰቀሰ። በዚህ ጊዜ በ797 ዓም የምስራቅቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጉባዔ አድርገው የቅዱሳንን ሥዕሎችማክበርና መሳም(መሳለም) እንደሚገባ ለሥዕሎቹም የአክብሮት ስግደት ማቅረብ ተገቢ መሆኑን በሰፊው አትተው ወስነዋል... ቀሪውን ከዌብሳይቱ ላይ ያንብብቡ
Updated on
Feb 8, 2024

Data safety

Safety starts with understanding how developers collect and share your data. Data privacy and security practices may vary based on your use, region, and age. The developer provided this information and may update it over time.
No data shared with third parties
Learn more about how developers declare sharing
No data collected
Learn more about how developers declare collection
Data is encrypted in transit
You can request that data be deleted

Ratings and reviews

4.5
546 reviews
Meron Walelighn
January 14, 2022
I love the amount of holy pictures in the app, 437 to be precise. But the amount of ads drove me crazy. Every 1 to 2 pictures there is a dumb ad from Facebook lite, instagram, and the damned virus cleaners. Let alone that, even the pictures are of extremly low quality. Terrible app, I must say.
30 people found this review helpful
Did you find this helpful?
Tsegazeab Gidey
August 23, 2021
Lot of add on every pictures. I can't even slide and see one pic without advertisements. I wish there are some ads.
40 people found this review helpful
Did you find this helpful?
yosef biyabiyen
June 20, 2021
It is good but there is an advert in every two pictures.
62 people found this review helpful
Did you find this helpful?

What's new

Sharing Holy Picture is now added
More Holy Pictures Added
Some bugs fixed specially for android 5+ users
bugfix